ውዱ ነብዬ

ዋቢ መጻሕፍት

- ቁርኣን ከሪም

- አንዋሩ ተንዚል – ቃዲ በይዳዊ

- ተፍሲሩ መዝሀሪ – ሰናኡላህ ፓኒፓቲ

- ተፍሲሩ ቁርጡቢ – ኢማም ቁርጡቢ

- ተፍሲሩ በይዳዊ – ቃዲ በይዳዊ

- ተፍሲሩ ከቢር – ፈኽሩዲን ራዚ

- ተፍሲሩ ኻዚን – ዐላኡዲን ባግዳዲ

- ተፍሲሩል ቁርኣን – ኢማም ቲርሚዚ

- ተፍሲሩል ቁርኣኒል ዐዚም – አቡል ፊዳ

- ሶሒሑል ቡኻሪ – ኢማም ቡኻሪ

- ሶሒሑ ሙስሊም – ኢማም ሙስሊም

- ሱነኑ ዳረቁጥኒ – ዳረቁጥኒ

- ሱነኑ ቲርሚዚ – ኢማም ቲርሚዚ

- ሙወጦእ – ኢማም ማሊክ

- ሙስተድረክ – ሐኪም ኒሳቡሪ

- ሱነኑ ኢብኒ ማጀ – ኢብኑ ማጀ

- ሱነኑ በይሀቂ – በይሀቂ

- ሱነኑ ዳውድ – አቡ ዳውድ

- አስ-ሱነኑ ሶጊር – ኢማም ነሳኢ

- ሙስነድ – በዛር

- ሙስነድ – ዳሪሚ

- ሙስነድ – አቡ የዕላ

- ሙስነድ – ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል

- ሶሒሕ – ኢብኑ ሒባን

- አኽባሩ መካ – አዝረቂ

- Birgivî Vasiyetnâmesi – İmâm-ı Birgivî

- ጃሊየቱል አክዳር – ማውላና ኻሊድ ባግዳዲ

- ጃሚዑል አሐዲስ – ሱዩጢ

- Cevâb Veremedi – Harputlu İshâk Efendi

- ደላኢሉ ኑቡዋ – አቡ ኑዐይም አል-ኢስፈሃኒ

- ደላኢሉ ኑቡዋ – በይሀቂ

- Dinî Sözlük – Türkiye Gazetesi

- አል-ቢዳያ ወን-ኒሃያ – ኢብኑ ከሲር (አቡል ፊዳ)

- አንሳቡል አሽራፍ – በላዙሪ

- አል-አንዋር – በገዊ

- አል-ኢክቲፋ ፊ መጋዚል ሙስጦፋ ወስ-ሰላሰቲል ኹለፋ – ኪላዒ

- አል-ለኣሊኡል መስኑዐ – ሱዩጢ

- አል-ሙዕጀሙስ ሶጊር – ኢማም ጠበራኒ

- አል-ሙሐበር – ኢብኑ ሐቢብ

- አል-ሙሰነፍ – ኢማም ዐብዱረዛቅ አስ-ሰንዓኒ

- አል-ሙሰነፍ – ኢማም ኢብኑ አቢ ሸይባ

- አል-ወፋ ቢ አሕዋሊል ሙስጦፋ – ኢብኑል ጀውዚ (ዐብዱረሕማን ጀውዚ / አቡል ፈረጅ ኢብኑል ጀውዚ)

- አውሷፉ ነቢ – ሱዩጢ

- ፈይዱል ቀዲር – ሙናዊ

- ፉቱሑል ቡልዳን – በላዙሪ

- Herkese Lâzım Olan Îmân – Hacı Feyzullah Efendi

- ሒልየቱል አውሊያ – አቡ ኑዐይም

- ኢሕያ – ኢማም ገዛሊ

- ኢንሳኑል ዑዩን – ኑሩዲን ዐሊይ አል-ሐለቢ

- አል-ኢሷባ – ኢብኑ ሐጀር አል-ዐስቀላኒ

- ኢስባቱ ኑቡዋ – ኢማሙ ረባኒ

- İslâm Âlimleri Ansiklopedisi – Türkiye Gazetesi

- አል-ኢስቲዓብ – ኢብኑ ዐብዲልበር

- ኢዕቲቃድናማ – ማውላና ኻሊድ ባግዳዲ

- ከሽፉል ኸፋ – ኢስማዒል ዐጅሉኒ

- Kısas-ı Enbiyâ – Ahmed Cevdet Paşa

- ኪምያኢ ሰዓዳት – ኢማም ገዛሊ

- Me’âricü’n-Nübüvve Tercümesi (Peygamberler Tarihi) – Altıparmak Muhammed Efendi

- መጅመዑ ዘዋኢድ – ሀይሰሚ

- መጋዚ – ዋቂዲ

- መክቱባቱ ኢማሚ ረባኒ – ኢማሙ ረባኒ

- መክቱባቱ መዕሱሚያ – ሙሐመድ መዕሱም ፋሩቂ

- አል-መዋሂቡ ለዱኒያ – ቀስጠላኒ

- Mevlid-i Şerîf (Vesîletü’n-necât) – Süleyman Çelebi

- Mir’ât-ı Kâinât – Nişancızâde Muhammed Efendi

- አል-ሙዕጀሙል ከቢር – ጠበራኒ

- ሙቀዲማ – ዳሪሚ

- አር-ረውዱል ኡኑፍ – ሱሀይሊ

- ሲራ – ኢብኑ ከሲር

- ሲረቱ ረሱል – ኢብኑ ኢስሓቅ

- አስ-ሲረቱን ነበዊያ – ኢብኑ ሂሻም

- ሲረቱ ነቢ – አሕመድ ኢብኑ ዘይኒ ደሕላን

- አስ-ሲየሩል ከቢር – ኢማም ሙሐመድ

- ሸርሑ ሲየሪል ከቢር – ኢማም ሰረኽሲ

- ሱቡሉል ሁዳ – ሸምሱዲን ሻሚ

- ሸማኢሉ ሸሪፍ – ኢማም ቲርሚዚ

- ሺፋኡ ሸሪፍ – ቃዲ ዒያድ

- ሸዋሂዱ ኑቡዋ – ማውላና ዐብዱረሕማን ጃሚ

- ሹዐቡል ኢማን – በይሀቂ

- ጠበቃቱል ኩብራ – ዐብዱልወሃብ አሽ-ሸዕራኒ

- ጠበቃቱ ሶሓባ – ኢብኑ ሰዕድ

- ታሪኹል ከቢር – ቡኻሪ

- ተኽሪጅ – ኹዛዒ

- ታሪኹ ዲመሽቅ (የደማስቆ ታሪክ) – ኢብኑ ዐሳኪር

- Tam İlmihâl Se’âdet-i Ebediyye – Hüseyin Hilmi Işık

- ታሪኹ ጠበሪ – ጠበሪ

- ታሪኹል ኢስላም – ኢማም ዘሀቢ

- አት-ተራቲቡል ኢዳሪያ – ከታኒ

- ኡስዱል ጋባ – ኢብኑል አሲር

- ዑዩኑል አሰር – ኢብኑ ሰይዲን ናስ

ዐብዱልሐሚድ ኻን II

«ይልዲዝ» አልበሞች። መካ – መዲና

ፎቶግራፎች

ካዕባ አሽ-ሸሪፋ – መካ አል-ሙከረማ የመስጂደል ሐራም መግቢያ በር

የሶፋ ኮረብታ – መካ የመርዋ ኮረብታ – መካ

ሱረይ ሁማዩን በመካ ዐብዱልሐሚድ ኻን I ያሠሩት የዘምዘም ጉድጓድ

መውሊዱ በይቲ ሸሪፍ (1909 እ.ኤ.አ.)

በትልቁ ፎቶግራፍና ከታች በቀኝ ባለው ፎቶግራፍ ቀኝ በኩል የሚታየው አንድ ጉልላትና አንድ ሚናራ ያለው መስጂድ ክቡር ረሱሉላህ ዓለምን በመምጣታቸው ያከበሩበት የተባረከ ስፍራ ነው።

ክቡር ነብያችን በሂጅራቸው ጊዜ ይህንን የተባረከ ቤት ለሰይዲና ዐሊይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ወንድም ለዐቂል ኢብኑ አቢ ጧሊብ አስረክበውት ነበር። የዐቂል የልጅ ልጆችም ለሐጃጅ ወንድም ለሙሐመድ ኢብኑ ዩሱፍ አስ-ሰቀፊ ሸጡት።

በኋላም ይህ የተባረከ ቤት በዐባሲዩ ኸሊፋ በሃሩን አር-ረሺድ እናት በእመቤት ኸይዙራን ተገዝቶ ወደ መስጂድ ተለወጠ።

ከዐባሲዮች በኋላ በማምሉኮች የተጠበቀው ይህ መስጂድ በኦቶማን ዘመንም በጥንቃቄ ተጠብቋል።

ቃኑኒ ሱልጣን ሱለይማን ኻን መስጂዱን እንደገና አሠሩት፤ ነብያችን የተወለዱበትንም ቦታ በብር ዘንጎች አጥር ውስጥ አስከለሉት።

ሱልጣን አሕመድ ኻን I ደግሞ በወርቅ የሕፃን አልጋ ቅርጽ ያሠሩትን የመቃም መቀመጫ በዚሁ አጥር ውስጥ አስቀመጡ።

በሱልጣኖቹ እናቶች በጥንቃቄ እንክብካቤ የሚደረግለት የዚህ መስጂድ ፍላጎቶችም በቤተ መንግሥቱ እመቤቶች ይሟሉ ነበር።

በዚህ ረገድ ትልቁን አገልግሎት የሰጡት የሱልጣን መሕመድ IV ባለቤት (የሙስጦፋ II እና የአሕመድ ኻን III እናት) አመቱላህ ራቢዓ ጉልኑሽ ሱልጣን ናቸው።

ይህ መስጂድ በታሪክ ውስጥ ብዙ ጊዜ ታድሷል።

በ1924 እ.ኤ.አ. በፈረሰው መስጂድ ቦታ ላይ በ1950 እ.ኤ.አ. በሸይኽ ዐባስ ቀጧን የተሠራው ቤት ከ1959 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የመካ ሕዝባዊ ቤተ መጻሕፍት ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።

የአጅያድ ምሽግ (1890 እ.ኤ.አ.)

በተቀደሱት ምድሮች የመጨረሻዎቹ የኦቶማን አሻራዎች – ባለ ምሰሶ መተላለፊያዎች

በይቱላህን የከበቡት የመጀመሪያዎቹ ጥላ መስጫዎች በሰይዲና ዑስማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ዘመን ተተከሉ። ከዚያም በዐባሲዩ ኸሊፋ በመህዲ የተሠሩት ባለ ምሰሶ መተላለፊያዎች በጊዜ ብዛት አረጁ።

ቃኑኒ ሱልጣን ሱለይማን መተላለፊያዎቹን በሚማር ሲናን አሳደሱ፤ ከዚህ እድሳት በኋላ በመተላለፊያዎቹ ላይ ጉልላቶች ተጨመሩ። ከሚማር ሲናን ተማሪዎች አንዱ የሆኑት ሚማር መሕመት አጋ በ1590 እ.ኤ.አ. በመተላለፊያዎቹ ምሰሶዎች ላይ አዳዲስ ጭማሪዎችን አደረጉ፤ ከእንጨት የተሠሩትን ምሰሶዎችና ቅስቶች በእብነ በረድ አደሱ።

በሱልጣን ዐብዱልዐዚዝና በዐብዱልሐሚድ ኻን II ዘመንም እንክብካቤ ተደርጎላቸዋል።

በ2014 እ.ኤ.አ. ካዕባን የማስፋፋት ፕሮጀክት አካል ሆኖ መተላለፊያዎቹ ከቦታቸው ተነቅለው በዐረፋ አቅራቢያ ወዳለ የግንባታ ቦታ ተወሰዱ። በ2016 እ.ኤ.አ. እንደገና በቦታቸው ተቀመጡ።

የመዲና ባቡር ጣቢያ

የሰይዲና ዑስማን ቱርቤ

ካዕባ አሽ-ሸሪፋ

የጀነቱል ሙዐላ መግቢያ

አንድ የኦቶማን የጥበቃ ጣቢያ – መካ አል-ሙከረማ

ቃኑኒ ያሠሩት የሱ ሐኒያ ምሽግ – መዲና አል-ሙነወራ

መዲና አል-ሙነወራ

መካ አል-ሙከረማ

1. የአጅያድ ምሽግ

የአጅያድ ምሽግ በሱልጣን ዐብዱልሐሚድ ኻን I ዘመን ካዕባን ለመጠበቅ፣ የሐጃጆችን ደኅንነትና የመካ ከተማን ሰላምና መከላከያ ለማረጋገጥ ከ1781 እስከ 1783 እ.ኤ.አ. ባሉት ዓመታት ተሠራ፤ በአንደኛው የዓለም ጦርነትም የቱርክ ጦር ሰፈር ሆኖ አገልግሏል። ይሁን እንጂ የኦቶማን መታሰቢያ የሆነው የአጅያድ ምሽግ በ2002 እ.ኤ.አ. እንዲፈርስ ተደረገ።

2. የዑመር ተራራ

3. የሂንድ ምሽግ፦ የሂንድ ምሽግም የመካን ደኅንነት ለማጠናከር በ1806 እ.ኤ.አ. በሱልጣን ሰሊም ኻን III ተሠራ።

መዲና አል-ሙነወራ

1. የኡሑድ ተራራ
2. የመጂዲያ ሚናራ

የመጂዲያ ሚናራ ባቡ ሰላምና ባቡ ረሕማ እንደሚባሉት የመስጂዱ ሌሎች ሚናራዎች ሁሉ በሱልጣን ዐብዱልመጂድ ኻን ተሠራ። ሚናራዎቹ የኦቶማንን የኪነ ሕንጻ ስልት ያንጸባርቃሉ። 3. ቁበቱ ሰዓዳ (ቁበቱል ኸድራእ – አረንጓዴው ጉልላት)፦ የግብጹ የቱርክመን ሱልጣን ሰይፉዲን ሷሊሕ ቀላዉን በሂጅራ 678 [1279 እ.ኤ.አ.] ዓመት በሑጅረቱ ሰዓዳ ላይ የአሁኑን ጉልላት አሠርተው በእርሳስ አስለበጡት። ጉልላቱ በሂጅራ 1253 [1837 እ.ኤ.አ.] በሱልጣን መሕሙድ ኻን II (ረሕመቱላሂ ዐለይሂ) ትእዛዝ አረንጓዴ ቀለም ተቀባ።

4. የረኢሲያ ሚናራ

የረኢሲያ ሚናራ በማምሉኮች ተሠርቶ በቃኑኒ ሱልጣን ሱለይማን ኻንና በመሕመድ ኻን IV ዘመን ታድሷል። ዋናው ሙአዚን በዚህ አዛን ስለሚያደርግ ይህ ዋና ሚናራ ረኢሲያ ይባላል።

5. የኻሊዲያ የጥበቃ ጣቢያ

6. ቂሽላይ ዐሳኪሪ ሻሃና (የኦቶማን ጦር ሰፈር)

4. የፉልፉል ምሽግ

የመካ ደኅንነት በቂ ሆኖ ስላልታየ የፉልፉል ምሽግ ከ1800 እስከ 1801 እ.ኤ.አ. ባሉት ዓመታት በሱልጣን ሰሊም ኻን III ተገነባ።

በ1885 እ.ኤ.አ. ዑስማን ኑሪ ፓሻ የመካ አሚር በነበሩበት ዘመን ወደ ሆስፒታል ተለወጠ።

ማሳሰቢያ፦

የሂንድና የፉልፉል ምሽጎችም ከአጅያድ ምሽግ በፊት እንዲፈርሱ ተደርጓል።

7. መስጂደል ገማማ

«ገማማ» በዓረብኛ ደመና ማለት ነው። ክቡር ነብያችንን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሚያጠላቸው ደመና ሰይዳችን ወደ መስጂደ ነበዊ በሄዱ ጊዜ እዚህ ይጠብቅ ስለነበር አካባቢው «የደመናው ስፍራ» ተባለ፤ መስጂዱም ይህንኑ ስም ያዘ። ክቡር ነብያችን የዒድ ሶላቶችን እዚህ ሰገዱ። መስጂዱ በሱልጣን ዐብዱልመጂድ ኻን ዘመን ታድሷል።

8. የሰይዲና አቡበክር መስጂድ

በአሁኑ ጊዜ በሰይዲና አቡበክር መስጂድ ውስጥ በሚገኘው የኦቶማን የጽሑፍ ሰሌዳ ላይ መስጂዱ ለመጨረሻ ጊዜ በሱልጣን ዐብዱልዐዚዝ ኻን እንደታደሰ ተጽፏል። ፎቶግራፉ የተነሣው ከዚህ እድሳት ጥቂት ዓመታት በኋላ ነው።

9. የሰይዲና ዐሊይ መስጂድ

ክቡር ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እዚህ የዒድ አል-ፊጥርን ሶላት አሰገዱ። ሰይዲና ዐሊይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) በኺላፋቸው ዘመንና ሰይዲና ዑስማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) በቤታቸው በተከበቡ ጊዜ የዒድ ሶላትን በዚሁ ቦታ አሰገዱ። ስለዚህም «የሰይዲና ዐሊይ መስጂድ» የሚል ስም ተሰጠው።

10. የፋጢመቱ ዘህራ የውኃ ሰቢል

ካዕባ – ሐረም ሸሪፍ

1. መቃሙ ማሊኪ
2. መቃሙ ሐነፊ
3. ሐጀሩል አስወድ
4. መቃሙ ኢብራሂም እና መቃሙ ሻፊዒ

5. የተባረከው የዘምዘም ጉድጓድ

6. መቃሙ ሐንበሊ

7. ሙወቂትኻና፦ ሙወቂቶች ጊዜንና የሶላት ወቅቶችን ለመወሰን የሚሠሩባቸው፣ በውስጣቸውም ወቅትን ለመወሰን የሚያገለግሉ መሣሪያዎችና የተስተካከሉ ሰዓቶች የሚገኙባቸው፣ አነስተኛ የከዋክብት መመልከቻን የሚመስሉ ሕንጻዎች ሙወቂትኻና ይባላሉ። ብዙውን ጊዜ በትላልቅ መስጂዶች አጠገብ ይገኛሉ። ሰዓቶቹን የሚያስተካክሉትና በተለይም የሶላት ወቅቶችን የሚወስኑት ባለሙያዎች ደግሞ ሙወቂት ይባላሉ፤ ወጪያቸውም በዋቅፎች ይሸፈናል። 8. ቤተ መጻሕፍት፦ ጀነት ማረፊያቸው የሆነው ሱልጣን ዐብዱልመጂድ ኻን በሂጅራ 1262 (1846 እ.ኤ.አ.) ዓመት በካዕባ ምሥራቃዊ ጎን ከጥንት የቀሩትንና እያንዳንዳቸው ስድስት ሜትር ዲያሜትር ያለው ጉልላት የነበራቸውን ሁለት ሕንጻዎች አንዱን ሙወቂትኻና፣ ሌላውን ደግሞ ቤተ መጻሕፍት እንዲሆኑ አስለወጡ [Mirâtü’l Haremeyn – Mirâtü’l Mekke፣ II፣ 770]። ዐብዱልመጂድ ኻን ለቤተ መጻሕፍቱ 3,653 ጥራዝ መጻሕፍትን ለገሡ።

አስ-ሶላቱ ሐውለል ካዕባ (በካዕባ ዙሪያ የሚሰገድ ሶላት)

ቁበቱ ሰዓዳ እና የረኢሲያ ሚናራ

1. የፋጢመቱ ዘህራ የአትክልት ስፍራ
2. የዑስማን ሚሕራብ ጉልላት

ንጽሕት የሆነችው የመዲና አል-ሙነወራ ከተማ

መስጂደ ነበዊ

የመናኻ አደባባይ (የግመል ገበያ)

የጀነቱል በቂዕ መቃብር

1. የኢማም ማሊክና የናፊዕ ቱርቤ

2. የሰይዲና ዐቂል ኢብኑ አቢ ጧሊብ (የነብያችን የአጎት ልጅ) እና የሰይዲና ዐብዱላህ ኢብኑ ጀዕፈር ጠያር (የነብያችን የአጎት የልጅ ልጅ፣ የጀዕፈር ጠያር ልጅ) ቱርቤ

3. የአዝዋጁ ሙጦሀራት ቱርቤ፦

በዚህ ቱርቤ ውስጥ ከሰይደቲና ኸዲጃና ከሰይደቲና መይሙና በስተቀር ሁሉም የነብዩ ባለቤቶች (ካፈቱ አዝዋጂ ሙጦሀራት) ተቀብረዋል። የሰይደቲና ዓኢሻ ቀብርም የሚገኝበት ይህ ቱርቤ በ1543 እ.ኤ.አ. በቃኑኒ ሱልጣን ሱለይማን ታድሷል።

4. የሰይዲና ኢብራሂም ኢብኑ ረሱሉላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ቱርቤ

ከነብያችን የራሳቸው ቤተሰብ በጀነቱል በቂዕ የተቀበሩት የመጀመሪያው ሰው ገና ሕፃን ሳሉ ያረፉት ልጃቸው ኢብራሂም ናቸው።

በጀነቱል በቂዕ የተቀበሩት የመጀመሪያው ሶሓቢይ ደግሞ ሰይዲና ዑስማን ኢብኑ መዝዑን ናቸው። 5. የበናቱ ነቢ ቱርቤ፦ እዚህ የክቡር ነብያችን ሴቶች ልጆች ሰይደቲና ሩቀያ፣ ሰይደቲና ኡሙ ኩልሱምና ሰይደቲና ዘይነብ (ረዲየላሁ ዐንሁንነ) ተቀብረዋል።

6. የሰይደቲና ፋጢማ ቢንት አሰድ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ቱርቤ

7. ሙርዲዐቱል ሙርሰሊን ሰይደቲና ሐሊማ አስ-ሰዕዲያ፦ እዚህ የክቡር ነብያችን ዐለይሂ ሰላም የጡት እናት ሰይደቲና ሐሊማ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ተቀብረዋል።

8. የሰይዲና ዑስማን ኢብኑ ዐፋን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ቱርቤ፦ የሦስተኛው ኸሊፋ የሰይዲና ዑስማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ቱርቤ በ1205 ዓመት በሶላሑዲን አል-አዩቢ ተሠራ። በኦቶማኖች ዘመን ደግሞ ታድሶ እንክብካቤ ተደርጎለታል። 9. የአህለል በይት ቱርቤ፦ በዚህ ቱርቤ ውስጥ ሰይዲና ዐባስ (የክቡር ነብያችን አጎት)፣ ኢማም ሐሰን አል-ሙጅተባ፣ ኢማም ዘይኑል ዓቢዲን፣ ኢማም ሙሐመድ ባቂርና ኢማም ጀዕፈር ሷዲቅ (ረዲየላሁ ዐንሁም) ተቀብረዋል።

10. የሰይደቲና ፋጢመቱ ዘህራ ቱርቤ
ማሳሰቢያ፦

በጀነቱል በቂዕ የክቡር ነብያችን አራት ሴቶች ልጆችና አንድ ወንድ ልጅ ተቀብረዋል። ዐብዱረሕማን ኢብኑ ዐውፍ፣ ሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ፣ ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ፣ ሱሀይብ ኢብኑ ሲናን፣ አቡ ሁረይራ፣ አቡ ሱፍያን ኢብኑ ሐርብ፣ ሰዕድ ኢብኑ ሙዓዝና ሱፍያን ኢብኑል ሐሪስ (ረዲየላሁ ዐንሁም) በጀነቱል በቂዕ ውስጥ ቦታቸው በፎቶግራፉ ላይ ያልተመለከተ የሶሓቦች ታላላቆች ሲሆኑ እዚያው ተቀብረዋል። መዲና በ1806 እ.ኤ.አ. በተወረረች ጊዜ በጀነቱል በቂዕ የነበሩት የመቃብር ድንጋዮችና ቱርቤዎች ፈረሱ። በሱልጣን ዐብዱልሐሚድ ኻን II ዘመን የመቃብር ድንጋዮቹ ታደሱ፤ ቱርቤዎቹም እንደገና ተሠሩ። ይህ ፎቶግራፍ የተነሣው ከዚህ ግንባታ በኋላ ነው።

ነገር ግን በ1926 እ.ኤ.አ. የኦቶማኖች የሐረመይን አገልግሎት ካበቃ በኋላ ጀነቱል በቂዕ ያንኑ ዕጣ ፈንታ ዳግመኛ ገጠመው።

የጀነቱል ሙዐላ መቃብር

1. የኸዲጀቱል ኩብራ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ቱርቤ፦ የክቡር ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ባለቤት የሰይደቲና ኸዲጃ (ረዲየላሁ ዐንሃ) በጀነቱል ሙዐላ የሚገኘው ቱርቤ በ1543 እ.ኤ.አ. በቃኑኒ ሱልጣን ሱለይማን፣ በመካው ናኢብ በዳውድ ፓሻ ቁጥጥር ተሠራ።

ከዚያ በፊት በቱርቤው ቦታ ላይ የእንጨት ሣጥን ነበር።

2. የአጅዳዱ ረሱሊላህ ቱርቤ፦ በዚህ ቱርቤ ውስጥ የክቡር ነብያችን አያት የዐብዱልሙጠሊብና የቅድመ አያታቸው የዐብዱ መናፍ ቀብሮች ይገኛሉ።

3. የአቡ ጧሊብ ቱርቤ

4. የውዱ ክቡር ነብያችን የተባረኩ እናት የአሚና (ረዲየላሁ ዐንሃ) መቃም የሆነው ቱርቤ

በጣም በታወቀው ዘገባ መሠረት የእናታችን አሚና ቀብር በአብዋ ነው። ነገር ግን በአንዳንድ ምንጮች ወደ ጀነቱል ሙዐላ እንደተዛወረም ተዘግቧል።

ማሳሰቢያ፦

እነዚህ ቱርቤዎች በ1879 እ.ኤ.አ. በሱልጣን ዐብዱልሐሚድ ኻን II እንዲታደሱ ተደረገ።

ኤውሊያ ቸለቢ በኦቶማን ዘመን በጀነቱል ሙዐላ የክቡር ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አያት፣ አጎት፣ የሌሎች ሶሓቦችና የእስልምና ታላላቆች የሆኑ ሰባ አምስት ቱርቤዎች እንደነበሩ ይጠቅሳሉ።

የዐረፋ ቀኝ ጎን፣ ወደ ቂብላ የሚመለከተው

በሚና የዒድ አል-አድሓ በዓል

(ኖቬምበር 13 ቀን 1880 እ.ኤ.አ.)

የሰይዲና ሐምዛ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በኡሑድ ተራራ የሚገኙት ቱርቤና መስጂድ

መስጂደ ጀበሊ ዐይኒያ፦ ይህ ሰይዲና ሐምዛ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ሸሂድ የሆኑበት ቦታ ነው። ረሱሉላህ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መሣሪያ ታጥቀውና የጦር ትጥቃቸውን ለብሰው እዚህ ሰገዱ።

ሚና

የሐሚዲያ መስጂድ – መካ

የሰይዲና አቡ አዩብ አል-አንሷሪ ቤት

የኦቶማን ጦር ሰፈር – መካ

የጦይባ የሕዝብ ገላ መታጠቢያ – መዲና

የረኢሲያ ሚናራ – መዲና

ባቡ ሰላም – መዲና

አንድ የኦቶማን የኪነ ሕንጻ ሥራ – መካ

መካ (በቀኝ በኩል ያለው መስጂድ ውዱ ነብያችን የተወለዱበት ቤት ነው።)